የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በጃፓን ዋና ከተማ ቶኪዮ መካሄድ ላይ ባለው በ33ኛዉ ኤዢያ፤ አረብ እና አፍሪካ የኢንቨስትመንት ፎረም ላይ የኢትዮጵያ ልዩ ኢኮኖሚ ዞኖችን ጸጋ በማስተዋወቅ ላይ ይገኛል፡፡
በኢትዮጵያ ልዩ ኢኮኖሚ ዞኖችና ነጻ የንግድ ቀጠና በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ላይ ለመሰማራት ፍላጎት ካሳዩ የጃፓን ባለሀብቶች ጋር በቶኪዮ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ውይይት ተካሂዷል ፡፡
በቶክዮ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በተካሄደው የ33ኛዉ ኤዢያ፤ አረብ እና አፍሪካ የኢንቨስትመንት ፎረም የተሳተፉ የጃፓን ባለሀብቶች ለቅድመ-ኢንቨስትመንት ጥናት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጡ ገለጹ፡፡
በአዳማ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን የሚገኘው አንቴክስ ቴክስታይል ኃ.የተ.የግ.ማ በ20 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ተጨማሪ የማስፋፊያ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን አስታወቀ፡፡